በተመድ ከተጠነሰሱ ዓለም አቀፍ የጾታ ፍትህ ንቅናቄዎች አንዱ ፣ 16 ቀናት የሚረዝመው ጾታ መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ትኩረት እንዲያገኙ የሚያሳስበው ዘመቻ ነው።በዚህ ዘመቻ ውስጥ ለዓመታት በንቃት ከተሳተፉት ወጣት ኢትዮጵያውያን የመብት ተሟጋቾች መካከል አንዷ ሀና ላሌ ናት።
በሀገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ውስጥ የጥብቅና እና ግንኙነት ባለሞያ የሆነችው ሀና ፣ ጥቃቶችን መግታት የሁሉም ሕዝቦች ግብ ሊሆን እንደሚገባ ትሟገታለች።