እስራኤል በሊባኖስ ላይ በምታካሂደው ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያኖች ተገድለዋል - በጎ አድራጎት ተቋም
Your browser doesn’t support HTML5
እስራኤል የሂዝቦላህን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት በሊባኖስ ላይ እያካሄደችው ባለችው የአየር ጥቃት ቢያንስ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን፣ ቤይሩት የሚገኝ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል። እኛ ለእኛ በስደት የተሰኘው በጎ አድራጎት ተቋም መስራች ባንቺ ይመር ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ እስራኤል ጥቃቱን አጠናክራ በቀጠለችበት ወቅትም አዳዲስ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሊባኖስ መግባት መቀጠላቸውን አመልክተዋል።