ትራምፕ እና ባይደን በዋይት ኃውስ ተገናኙ
Your browser doesn’t support HTML5
ባለፈው ሳምንት ምርጫውን ካሸነፉ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ዋሽንግተን የተመለሱት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን ጋራ ዋይት ሃውስ ውስጥ ተገናኝተው እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።
ጆ ባይደን ትረምፕን ወደ ዋይት ኃውስ የጋበዟቸው ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ ሲሆን በዛም እንደደረሱ “ዶናልድ እንኳን ደስ አለህ” ብለዋቸዋል።