"ነገ የሚፈጠረውን አናውቅም" በእየሩሳሌም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢራን ወደ 180 የሚጠጉ ሚሳዬሎችን ወደ እስራኤል ማስወጨፏን ተከትሎ ነዋሪዎች ወደተዘጋጁ የቦምፕ መጠለያዎች እንዲገቡ የሚያስጠነቅቅ የአደጋ ማስጠንቀቂያ በመላው ሀገሪቱ ተሰምቷል። ጥሪውን ሰምተው መጠለያ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች መካከል ከ30 ዓመት በላይ በእስራኤል የኖሩት አቶ ተስፋሁን እሸቱ እና ቤተሰባቸው ይገኙበታል። "ዛሬ ለሊትም ሆነ ነገ ምን እንደሚፈጠር አናውቅም" ያሉት አቶ ተስፋሁን ዛሬ በእየሩሳሌም የነበረውን ሁኔታ አጋርተውናል።