የመስቀል በዓል በዋሽንግተን ዲሲ

Your browser doesn’t support HTML5

በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት የደመራ በዓልን ትላንት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አክብረዋል። በአሉን ለማክበር በቤተክርስቲያኑ የታደሙ ምዕመናን እና የቤተክርስቲያናቱ አገልጋዮችም፣ በዓሉ ከሐይማኖታዊ ፋይዳው በተጨማሪ የኢትዮጵያዊነት እሴት የሚታይበት መሆኑን አመልክተው፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ መስቀሉ ባስተማረው መሰረት በሰላም፣ በእኩልነትና በፍቅር እንዲኖሩ ጠይቀዋል።