የፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ሥርዓተ-ቀብር ተፈፀመ

Your browser doesn’t support HTML5

ታዋቂው የፍልስፍና ምሁር ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል:: ከቀብራቸው በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀ ሥነ-ሥርዓት የሽኝት መርሃ-ግብር የተካሔደ ሲኾን ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የፕሮፌሰር አንድሪያስ አድናቂዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡ የሽኝት እና የቀብር ሥነ-ሥርዓቱን የተከታተለው ኬኔዲ አባተ አጭር ዘገባ አሰናድቷል፡፡