ትላንት አርብ ማምሻውን በየመን ሁቲ አማጽያን የተተኮሱ ሁለት ሚሳኤሎች በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ የምትጓዝና የላይቤሪያ ባንዲራን የምታውለበልብ እቃ ጫኝ መርከብን ዒላማ ያደረጉ ሲሆን፤ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያስከትሉ በአቅራቢያው መውደቃቸውን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
አርብ ዕለት ሁለት ሚሳኤሎች “ከመርከቡ አቅራቢያ ሲፈነዱ” ከኤደን በስተምስራቅ 240 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታይቷል በማለት የብሪታንያ ወታደራዊ ሃይል የእንግሊዝ የባህር ንግድ ተልዕኮ ማዕከል አስታውቋል።
ለጥቃቱ ሁቲዎች እስካሁን ድረስ ሃላፊነት ያልወሰዱ አልወሰዱም። ሆኖም፣ አማጽያኑ ጥቃት መፈጸማቸውን ለማስታወቅ ሰዓታት ወይም ቀናት ሊፈጅባቸው ይችላል።
አማጽያኑ እስራኤል በጋዛ በሐማስ ላይ የምታደርገውን ዘመቻ እንዲቆም ለማስገደድ ከእስራኤል፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ወይም እንግሊዝ ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦችን ዒላማ ያደርጋሉ። ይሁን እንጂ እስከዛሬ ድረስ ጥቃት የተፈጸመባቸው አብዛኞቹ መርከቦች ወደ ኢራን ያለፉትንም ጨምሮ ከግጭቱ ጋር አነስተኛ ወይም ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ማእከላዊ ዕዝ በዛሬው ዕለት በየመን ሁቲ ቁጥጥር ስር ባለ ግዛት ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጣሉን አስታውቋል።