የሱዳን ጦር ኃይል መሪ አብደል ፈታ አልቡርሀን ከባላንጣ ጦር አመራሮች ጋር ሲውዘርላንድ ላይ ሊደረግ በተቃደው የሰላም ንግግር ላይ እንደማይሳተፉ አስታወቁ ። ለመቶ ዓመታት መወጋትን እንደሚመርጡ ተናግረዋል ።
"ወደ ጄኔቫ አንሄድም ።ለመቶ ዓመታት እንዋጋለን " ሲሉ በደቡብ ሱዳን ለተገኙ ዘጋቢዎች ተናግረዋል አልቡርሀን ። የአልቡርሀን ወታደሮች ላለፉት 16 ወራት ወታደሮቻቸው የፈጥኖ ደራሹን ጦር ኃይል አባላት ሲፋለሙ መቆየታቸው ይታወሳል።
የህዝቦችን ስቃይ ለማቃለል እና ዘላቂነት ያለው የተኩስ አቁም ለማምጣት ያለመችው ዩናይትድ ስቴትስ ነበረች ነሐሴ 14 ላይ የሰላሙን ንግግር ስዊዘርላንድ ውስጥ ያስጀመረችው። የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ልዑካን በስፍራው ቢገኙም የሱዳን ጦር ኃይሎች በማዕቀፉ ደስተኛ ባለመሆናቸው በንግግሩ ላይ ሳይተፉ ቀርተዋል ። ይሁንና ከሸምጋዮች ጋር በስልክ ሲነጋገሩ ቆይተዋል።
ከዩናይትድ ስቴትስ በተጨማሪ ንግግሩ በሳውዲ አረቢያ እና ስዊዘርላንድ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ ግብጽ ፣ የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች የተዘጋጀ ሲሆን ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ፣ ሱዳን ውስጥ ህይወትን የማዳን እና ሰላምን የማላቅ የትብብር ቡድን ሲል የሰየመው ተቋም መስርቷል ።
ንግግሮቹ ካለ ተኩስ አቁም ስምምነት አርብ ዕለት ቢጠናቀቁም ፣ በዓለማችን ከአስከፊዎቹ አንዱ መሆኑ ከተነገረለት ሰብዓዊ ቀውስ ጋር እየታገለች ባለችው ሀገር ሁለት ቁልፍ መተላለፊያ መስመሮች በኩል ርዳታ በሚገባበት ሁኔታ ላይ ግን መሻሻል ታይቷል ።
አሰቃቂው ጦርነት ከ5 ሰዎች መካከል 1ኛው መኖሪያውን ለቆ እንዲሸሽ ያስገደደ ሲሆን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድሏል ። ከሀገሪቱ ህዝብ ግማሽ በላይ ፣ 25 ሚሊየን ያህል ህዝብ አጣዳፊ ርሃብ ተጋርጦበታል ። (ኤ ኤፍ ፒ ነው)