ትረምፕ ጠለፋው ላይ አተኩረዋል ፤ ሃሪስ የጉርሻ ክፍያ ቀረጥን ለማስወገድ ቃል ገብተዋል

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ካደረጉባቸው ድረ-ገጾች አንዱ ተጠልፎ እንደነበር አስታውቀዋል። ዝርዝሮች አሁንም ገና እየታወቁ ቢሆንም፣ ትረምፕ ለምክትል ፕሬዝደንትነት እጩነት የመረጧቸው ጄዲ ቫንስ ትላንት እሁድ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝደንታዊ እጩዎችን አጠንክረው የተቹባቸውን በርካታ ቃለ መጠየቆች ሰጥተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃሪስ እና አጋራቸው ቲም ዎልዝ ኢኮኖሚው ላይ በማተኮር ባደረጓቸው የምርጫ ዘመቻዎች ደጋፊዎቻቸውን መቀስቀስ ቀጥለዋል። የቪኦኤ ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግልሲያስ ተከታዩን ዘግባለች ደረጀ ደስታ ያቀርበዋል፡፡