አቶ ጌታቸው ረዳ በህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ አስታወቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እና የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ፓርቲያቸው ሊያደርግ ባቀደው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደማይሳተፉ ገለጹ፡፡

ፓርቲው በምርጫ ቦርድ ለመመዝገብ ያቀረበው ሰነድ “የተጭበረበረ ነው” ብለው የከሰሱት አቶ ጌታቸው፣ የምዝገባ ሒደቱንም እንደማይቀበሉት በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ተኽላይ ገብረ መድኅን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ “ህወሓት እንደ ድርጅት እንዲድን ጠቅላላ ጉባኤው አስፈላጊ ነው፤” ብለዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በልዩ ኹኔታ መዝግቦታል።