ዶክተር ቴዎድሮስ ወልደ መድኅንና ዶክተር አሰፋ ዳምጤ፣ በዌስካንሰን ግዛት ሚልዋኪ ከተማ ነዋሪ የኾኑ በዕድሜ ብቻ ሳይኾን በትምህርትም የካበቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
በግዛቲቱ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ የኖሩት አንጋፎች፣ በሚልዋኪ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያየ ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስን ፖለቲካዊ ኹነቶች በቅርብ የሚከታተሉት ኢትዮ-አሜሪካውያኑ፣ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሰባሰቡበትን ማኅበር መሥራቾችም ናቸው።
በተጨማሪም፣ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ፖለቲካዊ እና ሕዝባዊ ተሳትፎ እንዲያድግ የድርሻቸውን በመወጣትም ይታወቃሉ።
በቅርቡ ወደ ሚልዋኪ ያቀናው ሀብታሙ ሥዩም በተያያዥ ጉዳዮች ላይ አነጋግሯቸዋል፡፡