በገዜ ጎፋ የመሬት ናዳ የሟቾች አስክሬን አኹንም እየተፈለገ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በገዜ ጎፋ የመሬት ናዳ የሟቾች አስክሬን አኹንም እየተፈለገ ነው

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት ናዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስከነ ህይወታቸው ከተቀበሩ ከ10 ቀናት በኋላ አሁንም አስከሬኖችን እየተገኙ ነው።

ከናዳው ውስጥ አስክሬን ያገኙ ቤተሰቦች ሐዘናቸውን በለቅሶ ሲገልጹ፣ ሌሎች ደግሞ የሚወዷቸውን ቤተሰቦች አስክሬን ለማግኘት ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

የልጃቸውን አስክሬን ሲያፈላልጉ ሮይተርስ ያገኛቸው አቶ ጉባ ጉርባ፣ " ባለሥልጣቱን የማፈላለጉን ሥራ ለማቆም እየተናገሩ ስለሆነ ቅር ብሎኛል፡፡ ፍለጋዬን ለመቀጠል ያለኝ ቁርጠኝነት የማይናወጥ ነው። እስከሚያስፈልገው ጊዜ ድረስ እዚሁ እይቆያለሁ፡፡ ቤቴን እዚህ መገንባት ቢኖርብኝም እንኳ ፍለጋዬን እቀጥላለሁ። ሰውነቱ ቢበሰብስም አጥንቱን እፈልገዋለሁ። አጥንቱን ማግኘት ካልቻልኩ ኮቱን ላገኘው እችላለሁ። ያ ደስ ይለኛል” ብለዋል።

ሰኞ፣ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የጣለውን ከባድ ዝናም ተከትሎ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሠተ ድንገተኛ የመሬት ናዳ፣ እስካኹን የ257 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

/ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/