በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 229 ደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 229 ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

ይኽ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ የ229 ሰዎች አስክሬን መገኘቱን እና ፍለጋውም ተጠናቅሮ መቀጠሉን ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።

የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ማምሻውን በአወጣው መግለጫ፣ ቁጥሩ መጨመሩን እና ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስታውቋል።