አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ ሞያ የማብቃት መርሐ ግብር ይፋ ኾነ

Your browser doesn’t support HTML5

መንግሥት፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋራ በመተባበር፣ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የኮዲንግ ሞያ ሥልጠና ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

መርሐ ግብሩ፣ በርቀት የሥራ ዕድል የመፍጠር ጥረት አካል እንደኾነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ሰው ሥልጠናውን መውሰድ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡