ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ የተደረገው ውይይት በሰላም እና ጸጥታ ላይ ማተኮሩ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ዛሬ ሰኞ፣ በዐዲስ አበባ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪቃ አመራር ልህቀት አካዳሚ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋራ የተወያዩት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ አተኩረው መወያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የውይይት ግብዣውን ካልተቀበሉት መካከል የኾነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ በበኩሉ፣ “መንግሥት፣ የኢትዮጵያን ችግሮች በቁርጠኝነት እና በሐቀኛ ድርድር ለመፍታት ዝግጁነት የለውም፤” ሲል ያልተሳተፈበትን ምክንያት ገልጿል፡፡

በውይይቱ ላይ ከተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የኾኑትን የኢዜማንና የኢሕአፓን፣ እንዲሁም በውይይቱ ካልተሳተፉት ደግሞ የኦፌኮን አስተያየት በማካተት ኬኔዲ አባተ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡