የፕሬዝደንት ባይደን ራሳቸውን ከምርጫው ማግለል እና የባለሞያዎች አስተያየት

Your browser doesn’t support HTML5

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሁለት ባለሞያዎች ከሳምንታት በኋላ ቺካጎ በሚካሄደው የዴሞክራቲክ ፓርቲ ብሄራዊ ጉባኤ ምክትል ፕሬዘዳንት ካማላ ሃሪስ ፕሬዝደንታዊ ዕጩ ሆነው የመመረጥ ዕድል እንዳላቸው ተናግረዋል።

ሜሪላንድ ውስጥ በሚገኘው ሞርጋን ስቴት ዩንቨርስቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ፣ የዩናይድት ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ለአሜሪካ ፖለቲካ ጉልህ አስተዋጾ ማበርከታቸውን በመግለጽ አወድሰዋቸዋል።

በቅርቡ ራሳቸውን ከምርጫ እንዲያገሉ ሲደረግባቸውን የነበረውን ግፊት በማስታወስም፣”ውሳኔታቸው ለብዙ አሜሪካውያን እፎይታን የሚሰጥ ነው” ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ሌላው በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡን የሕግ ባለሞያ እና በዩ ኤስ አፍሪካ ተቋም ፕሬዝደንት ዶ/ር ታዲዮስ በላይ የባይደን ከፕሬዝደንታዊ ምርጫ ፉክክር ራሳቸውን ማግለል የሚተብቁት እንደነበር ገልጸዋል።