በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የአመያ ወረዳ፣ ባለፈው ሰኞ ተፈጸመ በተባለ የታጣቂዎች ጥቃት፣ 12 ሰዎች መገደላቸውንና የቆሰሉም መኖራቸውን፣ የወረዳው አስተዳደር እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ኦላና፣ “ጽንፈኛ የፋኖ ታጣቂዎች” ሲሉ የጠሯቸውን ኀይሎች ለጥቃቱ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
የወረዳው ነዋሪዎች፣ አካባቢው አሁንም ወደ መረጋጋት አለመመለሱን ሲገልጹ፣ የወረዳው አስተዳዳሪ ደግሞ፣ ተጨማሪ የመንግሥት ኀይሎች መሰማራታችውን ተከትሎ ወረዳው በአንጻራዊ ሰላም ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ከጉራጌ ዞን የመጡ ናቸው ያሏቸውን ጥቃት አድራሾችም በቁጥጥር ሥር ለማዋል፣ ከዞኑ ባለሥልጣናት ጋራ በንግግር ላይ መኾናቸውንም ጠቁመዋል።