በኩመር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ጥቃት 10 የፖሊስ አባላት መገደላቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ጎንደር ዞን በሚገኘው የኩመር የስደተኞች መጠለያ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ የፌደራል ፖሊስ ጣቢያ ላይ፣ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ 10 የፖሊስ አባላት ሳይገደሉ እንዳልቀሩ መረዳቱን፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በምኅጻሩ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ፡፡

በመጠለያው የሚኖሩ ስደተኞችም፣ ትላንት ረቡዕ ንጋት ላይ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ መጠለያውን ሲጠብቁ የነበሩ የጸጥታ ኀይሎች መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ፣ ከዐማራ ክልላዊ መንግሥት ኃላፊዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡