ተመራቂ ሴቶችን ሥራ ፈጣሪ ያደረገው መርሐ ግብር

Your browser doesn’t support HTML5

በትምህርት ጥራት እና በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ላይ የሚሠራው ገባሬ ሠናዩ “አይዞን ፋውንዴሽን”፤ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋራ በመኾን ለሦስት ወራት ሲሰጥ የቆየውን “ሺ ካን” (ትችላለች) የተሰኘውን የወጣት ተመራቂ ሴት ተማሪዎች መርሐ ግብሩን ከሰሞኑ አጠናቋል። የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ሴቶች፣ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ትምህርታቸውን በ2015 ዓ.ም. አጠናቀው የተመረቁ ሲኾኑ፣ በሥራ ትስስር፣ በሥራ ፈጠራና በሥራ ፍለጋ ክህሎት ሥልጠናዎችን ወስደዋል።

በመርሐ ግብሩ ማብቂያ ላይ፣ የሥራ ፈጠራ ሐሳቦቻቸውን ካጋሩት የተለያዩ ቡድኖች መካከል፣ አንዱ ቡድን የ1ነጥብ5 ሚሊዮን ብር የሥራ ማስጀመሪያ ተሸላሚ ኾኗል።

ኤደን ገረመው፣ ተሳታፊዎቹንና የአይዞን ፋውንዴሽን መሥራች እንዲሁም ሥራ አስፈጻሚ የኾኑትን ሻሎም ያቆብ ኣርአያን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።