የውሃ ጥም ላራቆታቸው ከተሞች ተስፋ

Your browser doesn’t support HTML5

ስር የሰደደው የውሃ እጥረት ተጨማሪ የኑሮ ፈተና ለሆነባቸው የበርካታ ኢትዮጵያ ከተሞች ነዋሪዎች ተስፋ ፈጥኖ የማይከሰት የሩቅ ሕልም ነው።

የአቅርቦት እና ፍላጎት ያለመመጣጠን፣ ያልተማከለ የውሃ ክፍፍል እና ዋጋ፣ የከርሰ ምድር ውሃ ከሚገባው በላይ መራቆት ከቀዳሚው ምክንያቶች ውስጥ መሆናቸውን የሚናገሩት ከፍተኛ የውሃ ጉዳይ አዋቂዎች፤ የተለያዩ የውሃ ምንጮችን መጠቀምን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚያግዝ .. “አፋጣኝ እርምጃ የሚሻ ጥሪ” ያሉትን ፍኖተ ካርታ አቅርበዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ የውሃ ጉዳይ አዋቂዎች ዶ/ር ጥሩሰው አሰፋ እና ዶ/ር ፈቃዱ ሞረዳ በአንድ የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ላይ የቀረበውን የፖሊሲ ጥናት ጽሁፋቸውን ይዘት እና አጠቃላዩን የውሃ ችግር እና መፍትኄ ይፈትሻሉ።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ጉዳዮች በሚደረጉ ጥናቶች ባለሞያዎችን የሚያሳትፈው “ዊአስፓየር” የበጎ አድራጎት ድርጅታቸው ተጠሪ አቶ ሳምሶን ደምሴ ተፈራ በውይይቱ ይቀላቀሏቸዋል።