ጣሊያን ወደ አገሯ የሚጎርፈውን ፍልሰተኛ መከላከል የሚያግዝ ዐዲስ ዘዴ ሥራ ላይ ልታውል ነው

Your browser doesn’t support HTML5

የጣሊያን መንግሥት በልማት ላይ ያተኮረ ዐዲስ ፕሮግራም ተግባር ላይ በማዋል ስደተኞች ከአፍሪካ ተነስተው የሜዲትራኒያንን ባህር ለመሻገር የሚያደጉትን ጉዞ ለመከላከል እየሞከረ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት እቅዱ ከሠራም መላው አውሮፓ በጥሩ ምሳሌነት ሊጠቀምበት የሚችል ነው።

ሄንሪ ዊልከንስ ከጣሊያኗ የላምፔዱሳ ደሴት ለአሜሪካ ድምጻ ባጠናቀረው ዘገባ ባለፈው ዓመት በአንዲት ሳምንት ዕድሜ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ባሕሩን አቋርጠው እዚያ ሲደረሱ ያዩ የአካባቢው ነዋሪዎችም አዲሱን ርምጃ በይሁንታ መቀበላቸውን እየገለጹ ነው።