የፈረንሣዩ ምርጫ ያልተጠበቀ ውጤት የፈጠረው አጣብቂኝ

Your browser doesn’t support HTML5

በፈረንሣይ፤ ከቀኝ ክንፍ ወግ አጥባቂው ይልቅ ግራ ዘመሙ ፓርቲ ባለፈው እሁድ ምርጫ የበላይነቱ መያዙን ተከትሎ፣ መንግስት ወደፊት የሚቀጥልበትን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት ውይይት ተጀምሯል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ ሶስት ሳምንታት ሲቀረው በተደረገው የእሁዱ ምርጫ የትኛውም ፓርቲ መንግስት ለመመሥረት የሚያስችል ወሳኝ የበላይነትን ሳይይዝ ቀርቷል::

የቪኦኤዋ ሊሳ ብራያንት ከመዲናዋ ፓሪስ ወጣ ብላ ከምትገኘው ኑዪ ፕሌዛንስ የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።