የፕሬዝደንት ባይደን ብቃት ጥያቄ ባስነሳበት የኔቶ ጉባኤ ተጀምሯል

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባላት፤ ዩክሬን የመከላከያ አቅሟን በምታጎለብትበት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ጉባኤ ጀምረዋል፡፡ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንም የቃል ኪዳን ድርጅቱ ዓባል ሃገራት መሪዎችን ተቀብለዋል።

አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ ጉባኤው ከዩክሬን ጉዳይ በተጨማሪም፣ ጆ ባይደን በኅዳሩ ምርጫ ቢሸነፉ ቃል ኪዳኑን ከትረምፕ ተጽእኖ ነጻ በሚያደርጉበት መንገድ ላይ ይነጋገራል።

የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማረኛ መልሶታል።