የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ግድያ ተከትሎ ለጸጥታ ችግሮች መፍትሔ እንዲፈለግ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የሚታዩትየጸጥታ ችግሮች እና ተያያዥ ኹኔታዎች መፍትሔ እንዲበጅላቸው፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እናየሃይማኖት አባቶች ጥሪ አቅርበዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ ዓሊ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ በነዋሪዎች ዘንድ የደኅንነት ስጋት መፈጠሩንም፣ ጥሪ አቅራቢዎቹ አመልክተዋል።

በዞኑ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብደላ አሕመድ፣ የዋና አስተዳዳሪው ግድያ አሁንም በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።