በጎሮ ዶላ ወረዳ የታጣቂዎች ጥቃት የሞት እና የአካል ጉዳት ደረሰ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ጎሮ ዶላ ወረዳ፣ ማንነታቸው ያልተለየ ታጣቂዎች፣ በሕዝብ የትራንስፖርት መገልገያ ላይ ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ አንድ ሰው ሲሞት ሦስት ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ ነዋሪዎቹ እና የሆስፒታል ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጡ መቀጠሉንም ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።