በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ገለጸች

Your browser doesn’t support HTML5

ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋራ የተደረገውን የመግባቢያ ስምምት በተመለከተ፣ በማኅበራዊ የመገናኛ አማራጮች የሐሰት መረጃዎች እየተሰራጩ ናቸው፤ ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡

“ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነቱን ለመሰረዝ እንደወሰነች” የሚገልጽ ይዘት ያለው መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ፣ ትላንት ረቡዕ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ፣ የመግባቢያ ስምምነቱ የሚገኝበትን ደረጃ በተመለከተ “ወቅቱ ሲደርስ ይገለጻል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ቃል አቀባዩ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ግዛት ጥሰው እንደገቡ፣ በሶማሊያ በኩል የቀረበውን ክስም “ሐሰት ነው” ሲሉ አጣጥለዋል፡፡