በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ተስፋፍቷል የተባለ አሠቃቂ ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል፣ በሴቶች ላይ ተበራክቷል የተባለው እገታ፣ ግድያ እና ጾታዊ ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ በመቐለ ከተማ ተካሔደ፡፡

በሺሕዎች የሚቆጠሩት ሴት ሰልፈኞቹ፣ “መንግሥት ጸጥታን ያስከብር፤ ለተበዳዮችም ፍትሕ ይስጥ” ሲሉ ተሰምተዋል፡፡

ለሰልፈኞቹ ምላሽ የሰጡት፣ የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሓዱሽ ተስፋ፣ በክልሉ በተለይ በሴቶች ላይ አሠቃቂ እና በጭካኔ የተሞሉ ያልተለመዱ ጥቃቶች መበራከታቸው አሳዛኝ መኾኑን ገልጸው፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ፣ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ትላንት ሰኞ በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ሥርዐተ አልበኝነት መንገሡን በመጥቀስ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በድክመት ወቅሰዋል፡፡