የትግራይ ተፈናቃዮች ከሰኔ 30 ቀን በፊት ወደቀዬአቸው ለመመለስ በድጋሚ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል የተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ የጠየቁበትን ሰላማዊ ሰልፍ፣ ትላንት እሑድ አካሒደዋል፡፡

በመቐለ ከተማ ሰልፍ የወጡ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች፣ መንግሥት ቃል በገባው መሠረት፣ ከሰኔ 30 ቀን በፊት ወደ ቀዬአችን ይመልሰን፤ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በሰልፉ ላይ፣ ተፈናቃዮች በተደጋጋሚ ሰልፍ መውጣታቸውን ያወሱት፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ “የአሁኑ ሰልፍ የመጨረሻ ይኾናል፤” ብለዋል፡፡

የተፈናቃዮቹን አመላለስ ያለጸጥታዊ ችግር ለመፈጸም እንደሚሠራ ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል፡፡