በኖኖ ወረዳ የሠርግ ላይ ጥቃት ሙሽሮችን ጨምሮ 27 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች 17 መቁሰላቸውን፣ በወረዳው የቢፍቱ ጃለላ ቀበሌ አስተዳዳር እና ተጎጂዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ጥቃቱ የደረሰበት የጊፍቲ ጃለላ ቀበሌ ሊቀ መንበር አቶ ነስሩ ዑመር፣ በዕለቱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ በተወረወረው ቦምብ እና በተከፈተው ተኩስ ከተገደሉት ውስጥ ተጋቢ ሙሽሮችም እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ የተፈናቀሉት የቀበሌው ነዋሪዎች በችግር ላይ እንደሚገኙ ያመለከተው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ወንጀሉን የሚያጣራ ቡድን ወደ ቦታው ለመላክ እየተዘጋጀ መኾኑን አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።