የከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃዎች የቃታ አጠቃቀም እገዳ ተቀለበሰ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃዎች፣ እንደ መትረየስ አከታትለው ጥይት እንዲተኩሱ የሚገጠመው ማቀባበያ ቃታ ጥቅም ላይ እንዳይውል የከለከለውን እገዳ፣ ባለፈው ሳምንት ቀልብሶታል።

የአሜሪካ ድምፁ ስካት ስተርንስ ባጠናቀረው ዘገባ እንዳመለከተው፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመሣሪያ እና የመሣሪያ ባለቤትነት ጉዳይ፣ በመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዐቢይ ጉዳይ ኾኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።