በአፋር እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ በአገረሸው ግጭት ሰብአዊ ጉዳት መድረሱን፣ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም፣ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ እያሰለሰ የቀጠለው በጦር መሣሪያ የተደገፈ ግጭት እያስከተለ ያለው ጉዳት እንዳሳሰበው፣ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ያገረሸውን ግጭት ለማስቆም የፌደራል መንግሥት እየሠራ መኾኑን ገልጾ፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡