በጅጋ ከተማ በቀጠለ ግጭት ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ጅጋ ከተማ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ፣ በመንግሥት እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል የተነሣውን ግጭት ተከትሎ፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

ጅጋን ከተማና የአካባቢው ሕዝብ በመወከል የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በበኩላቸው ሲቪሎች መገደላቸውን ገልጸው፤ ጉዳዩን ለአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።