ሚዛን ወጣት የሕግ ባለሞያዎች ማዕከል፣ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በወጡ የሕግ ምሩቃን የተመሠረተ የበጎ ፈቃደኞች ስብስብ ነው፡፡
የማዕከሉ የሕግ ባለሞያዎች፥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች፣ የወንጀል እና ፍትሐ ብሔር ጉዳዮችን ጨምሮ፣ በማናቸውም የሕግ ጉዳዮች ላይ በነጻ የማማከር እና ጥብቅና የመቆም አገልግሎትን ይሰጣሉ።
በተጨማሪም፣ ለየት ባለ መልኩ በሐዋሳ ከተማ ለማኅበረሰብ ጠንቅ በኾኑ ሁለት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ፣ ለሕዝብ ጥቅም በመሟገት ለውጥ ማምጣታቸውን፣ የማዕከሉ ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዐማኑኤል ድባቤ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ኤደን ገረመው፣ አቶ ዐማኑኤልንና የማዕከሉን የሕግ አገልግሎት የሚጠቀሙ እናትን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።