ትረምፕ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን በይግባኝ ለማስቀልበስ ይሻሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በእ.አ.አ 2016 ከተካሄደው ምርጫ ቀደም ብሎ፣ ‘ለአንዲት የወሲብ ፊልም ተዋናይ ግንኙነታቸውን ይፋ እንዳታወጣ አፍ ማዘጊያ ገንዘብ ከፍለዋል፣ ወጪውንም ለመደበቅ በንግድ ዶሴዎቻቸው ላይ በተጭበረበረ መንገድ አስፍረዋል’ በሚል በቀረበባቸው ክስ፣ ባለፈው ሳምንት በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን ይግባኝ እንደሚጠይቁበት አስታውቀዋል።

የቪኦኤው ስካት ስተርንስ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት የይግባኝ ሁኔታ ምን ሊመስል እንደሚችልና፣ የጥፋተኝነት ፍርዱ ከምርጫው በፊት ይቀለበስ እንደሁ ተመልክቷል። እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።