የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶር. ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ ዐዋጁ አገራዊ ምክክሩን ታሳቢ በማድረግ መሻሻሉን ገልጸዋል፡፡ በዚኽም፣ ህወሓት እና በዐመፅ ተግባር ሲሳተፉ ነበሩ የተባሉ ፓርቲዎችን፣ እንዲሁም በትጥቅ ግጭት ውስጥ ያሉ ቡድኖችን ወደ ምክክር ሒደቱ ለማምጣት መታለሙን ተናግረዋል፡፡ በዐዋጁ ማሻሻያ ላይ፣ ከምክር ቤት አባላት የድጋፍ እና የተቃውሞ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡
ፓርቲዎች ዳግም ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የሚያስችል የዐዋጅ ማሻሻያ ጸደቀ
Your browser doesn’t support HTML5
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዐመፅ ተግባር ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ፓርቲዎች ዳግም ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የሚያስችል የዐዋጅ ማሻሻያ ዛሬ አፀደቀ።