በምዕራብ ጉጂ ዞን ግጭት አራት ሰዎች መገደላቸውን ወረዳው አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ጉጂ ዞን ሱሮባርጉዳ ወረዳ፣ በሸማቂዎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ፣ አንድ ሲቪል ሰውን ጨምሮ አራት ሰዎች መገደላቸውን፣ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የሱሮባርጉዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ዱጎ፣ ሌሎች ሁለት ሲቪሎች መቁሰላቸውንና ሁለት ታጣቂዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

በስፍራው ነበርኹ ያሉ አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ታጣቂዎች አንድ ሰው ከተሽከርካሪ ላይ አስወርደው መግደላቸውን ተናግረዋል፡፡