የምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አርሶ አደሮች የአዝመራ ጊዜ “እያለፈን ነው” አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በመንግሥት ታጣቂዎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የቀጠለው ግጭት ከቀዬአቸው እንዳፈናቀላቸው የገለጹ፣ የምዕራብ እና የቄለም ወለጋ ዞኖች አርሶ አደሮች፣ በዚኽም ምክንያት የአዝመራ ወቅት እያለፋቸው መኾኑን ተናገሩ።

በዓመቱ ውስጥ የቀጠሉት የተኩስ ልውውጦች የአካባቢውን የግብርና እንቅስቃሴ እያስተጓጎሉ መኾናቸውን የገለጹት አርሶ አደሮቹ፣ በእርሻቸው ላይ መሥራት ባለመቻላቸው ለቀጣዩ ዓመት ስጋት እንዳደረባቸው በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በአርሶ አደሮቹ አስተያየት ላይ፣ ከምዕራብ እና ከቄለም ወለጋ ዞኖች ግብርና ጽሕፈት ቤቶች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።