በክልሎች ደረጃ የሚደረገው የምክክር ምዕራፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ በዛሬው ዕለት፣ ከ2ሺሕ5መቶ በላይ የኅብረተሰብ ተወካዮች ይሳተፉበታል የተባለውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ምዕራፍ አስጀምሯል።

በአድዋ መታሰቢያ ሙዝየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተዘጋጀውን የምክክር መድረክ በንግግር የከፈቱት፣ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፣ “ሀገራዊ ምክክሩ ወደ ከፋ ችግር እንዳንገባ ያስችለናል፤” ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ የአሜሪካ ድምፅ የጠየቃቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ፣ የምክክር ሒደቱን በመቃወምና በመደገፍ የተለያዩ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል፡፡ የምክክር ምዕራፉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ መድረኩ፥ “የታፈኑ ሐሳቦች የሚስተጋቡበት ይኾናል፤” ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ ገብረ ሚካኤል ገብረ መድኅን ዝርዝር አለው፡፡