በአሜሪካ በየአራት ዓመቱ በበጋው ወቅት ሁለቱ ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎቻቸውን ያቀርባሉ። በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር፣ በዊስካንሰን ግዛት ሙልዋኪ ከተማ የሚገኙ ሪፐብሊካኖች የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጩ አድርገው የሚያቀርቡ ሲሆን፣ በወሩ ደግሞ ቺካጎ ላይ ዲሞክራቶች አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እጩ መሆን ይፋ ያደርጋሉ። ሌላው ብዙ ትኩረት ያልተሰጠው ግን፣ በመጪው ቅዳሜ ምሽት በሚካሂደው ጉባዔ ፕሬዚዳንታዊ እጩውን የሚያቀርበው ሌላው ፓርቲ ነው። የአሜሪካ ድምፅ ብሔራዊ ዘጋቢ ስቲቭ ኸርማን ከዋሽንግተን ያደረሰንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።