መንግሥት የግል አየር መንገዶች መደበኛ በረራ እንዲጀምሩ ፈቀደ

Your browser doesn’t support HTML5

መንግሥት፣ የግል አየር መንገዶች፣ በሀገር ውስጥ መደበኛ በረራ እንዲጀምሩ መፈቀዱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን፣ ለሀገር ውስጥ አየር መንገዶች በጻፈው ደብዳቤ፣ “ሀገር በቀል የአየር ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች በአሁኑ ጊዜ እየሰጡት ካለው የቻርተር በረራ በተጨማሪ፣ መደበኛ የመንገደኞች እና የጭነት በረራ አገልግሎቶች መስጠት እንዲችሉ” መፍቀዱን ይገልጻል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአቪዬሽን ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኀይሉ በበኩላቸው፣ ይህ ውሳኔ በሌሎች ድጋፎች ካልታገዘ፣ ብቻውን አየር መንገዶቹን መደበኛ በረራ እንዲጀምሩ አያስችላቸውም፤ ብለዋል፡፡

የአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት ማኔጂንግ ዲሬክተር ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ደግሞ፣ የግል አየር መንገዶች፣ መደበኛ በረራ ለማካሔድ ፈቃድ ብቻ ሳይኾን ዐቅምም ያስፈልጋቸዋል፤ ባይ ናቸው፡፡ “በሀገር ውስጥ ብቻ ብረሩ” የሚል ፈቃድ፣ ለአየር መንገዶቹ እንደማይጠቅምም አስገንዝበዋል፡፡ በአቪዬሽን ዘርፉ ልዩ ልዩ ችግሮች መኖራቸውን ያመለከቱት ካፒቴን ሰሎሞን፣ ዘርፉ እንዲሻሻል ከተፈለገ “የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጣልቃገብነት” ይፈልጋል፤ ብለዋል፡፡