የዓለም መሪዎች በራይሲ ሞት የተሰማቸውን ኀዘን በመግለጽ ላይ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካ በራይሲ ሞት የተሰማትን ኀዘን ብትገልጽም፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዛቸውን ነቅፋለች፡፡

የዓለም መሪዎች፣ የኢራኑ ፕሬዚዳት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያን፣ በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸውን በማጣታቸው የተሰማቸውን ኀዘን በመግለጽ ላይ ናቸው።

የፓኪስታን፣ ሩሲያ እና ሊባኖስ መሪዎች፣ ራይሲ የተከበሩ መሪ እንደነበሩ ሲገልጹ፣ አሜሪካ ግን “አስከፊ” ብላ የገለጸችው የሰብአዊ መብቶች አያያዛቸው መታወስ እንዳለበት አስታውቃለች፡፡

የቪኦኤ የኮንግረስ ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።