በጋዛ ትምህርትንና ሕክምናን የማዳረስ ጥረት

Your browser doesn’t support HTML5

በእስራኤል ከባድ የቦምብ ጥቃት ሥር በምትገኘው ጋዛ ውስጥ፣ 72ነጥብ5 ከመቶ የሚኾኑ ትምህርት ቤቶች፣ ሙሉ እድሳት አሊያም መልሶ ግንባታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ አመልክቷል።

ጋዛ እና በእስራኤል የተያዘችው ምዕራባዊ ዳርቻ(ዌስት ባንክ)፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ተማሪዎች መፍለቂያዎች ናቸው። ቀደም ሲል ትምህርታቸውን አጠናቀው መደበኛ ሕይወት በመምራት ላይ የነበሩ የሕክምና ተማሪዎች፣ በየዕለቱ የሚጨምረውን የሕክምና ርዳታ ፍላጎት ለመደገፍ በበጎ ፈቃድ እያገለገሉ ናቸው። በተጨማሪም ወጣቶች እና መምህራን፣ ሕፃናትን ሰብስበው በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

በሮይተርስ የተጠናቀረውን ዘገባ ኤደን ገረመው ወደ አማርኛ መልሳዋልች።