እነትራምፕ ለእስራኤል የጦር መሣሪያ እንዳይላክ በተላለፈው እግድ ባይደንን ተቹ

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በቅርቡ ወደ እስራኤል ሊላክ የነበረን የጦር መሣሪያ ለጊዜው እንዲታገድ አድርጋለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ደግሞ የጋዛው ጦርነት፣ በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻ ላይ ጎልተው የሚሰሙ የጦፉ ንግግሮች አካል ኾኗል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ጉዳዩን አስመልክቶ የያዙትን አቋም የተቹት የፖለቲካ ተቀናቃኛቸው የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ፣ አንዳንድ የፓርቲያቸውን አባላት ተቀላቅለዋል።