የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ፋኖ “የሰላም ጥሪ አልተደረገልንም” አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና የአማራ ታጣቂ ፋኖ፣ የኢትዮጵያ ኹሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ወደ ሰላም ሊያመጣ የሚችል ሕጋዊ ተቋም መኾኑን እንደማይቀበሉት፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሁለቱም አካላት፣ ኮሚሽኑ ሲዋቀር አንሥቶ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አለማድረጋቸውን፤ እንዲሁም ኮሚሽኑ በመንግሥት በጀት የሚንቀሳቀስ መኾኑን በመጥቀስ፣ በገለልተኛነቱ ላይ ጥያቄ አንሥተዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ሕጋዊ በኾነ መልኩ በደብዳቤም ይኹን በኢ-ሜይል በምክክር መድረኩ ላይ እንዲሳተፉ አለመጋበዛቸውን፣ ተወካዮቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።