በኢትዮጵያ የቅድመ ክስ እስር ሁኔታ እንደሚያሳስበው ኮሚሽኑ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የፍርድ ቤትን የዋስትና ትእዛዝ አለማክበርን ጨምሮ በቅድመ ክስ ሒደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እንደሚያሳስቡት ኢሰመኮ አመልክቷል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሞያዎች አቶ አምኃ መኰንንና አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ የጉዳዩን አሳሳቢነት ጠቅሰው፣ ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ በኋላ ደግሞ የተራዘመ እስርን የመሳሰሉ በቅድመ ክስ የሚስተዋሉ ክፍተቶች መባባሳቸውን ተናግረዋል።

በዚኽ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ የመንግሥት አካላት ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት የተደረጉ ሙከራዎች ባይሳኩም፣ መንግሥት አብዛኛውን ክሶች በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ተደምጧል።