የባይደን ምርጫ ቡድን በፍሎሪዳ ለወጣው አዲስ የውርጃ ሕግ ትረምፕን ተጠያቂ አድርጓል

Your browser doesn’t support HTML5

ጽንስ ስድስት ሳምንት ከሆነው በኋላ ውርጃ እንዳይፈጸም የፍሎሪዳ ግዛት አዲስ ሕግ ደንግጓል። እየተካሄደ ባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዘመቻ፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሥነ ተዋልዶን መብት በተመለከተ ግዛቶች የየራሳቸውን ውሳኔ እንዲሰጡ በመደገፍ ላይ ናቸው።

ጆ ባይደን በበኩላቸው፣ የስነ ተዋልዶ መብትን የመወሰን ስልጣን ለየግዛቶቹ የሚሰጥ ከሆነ፣ የሴቶችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል ባይ ናቸው።