ለኅትመት ውጤቶች ንባብ መዳከም የመጻሕፍት ዐውደ ርእይ እንደ መፍትሔ

Your browser doesn’t support HTML5

እንደ ማኅበራዊ ብዙኀን መገናኛ ያሉ የዘመኑ የመረጃ እና ተግባቦት መተግበሪያ ቴክኖሎጂዎች፣ በኅትመት ውጤቶች ንባብ ላይ ተጽእኗቸው እየጎላ እንደመጣ ይታመናል።

የመጻሕፍት ንባብ ባህልን ለማዳበር የሚያስችሉ አማራጮችን በመጠቀም የቴክኖሎጂውን አሉታዊ ጫና መቋቋም እንደሚያስፈልግ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ይመክራሉ፡፡

ኬኔዲ አባተ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጅቶ ለአንድ ሳምንት ሲካሔድ በቆየውና ከትላንት በስቲያ እሑድ በተጠናቀቀው የመጻሕፍት ዐውደ ርእይ ላይ ያገኛቸውን ገዥዎች እና ሻጮች አስተያየት በማካተት ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡