የኢትዮጵያ መንግሥት የባለድርሻዎችን ተሳትፎ በማሳደግ ቀውሶችን ለመፍታት ቃል ገባ

Your browser doesn’t support HTML5

በጄኔቫ በተደረገው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይ ኹነኛ አስተዋፅኦ ሊያደርግ የሚችል ድጋፍ መገኘቱን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

ኾኖም በተደራራቢ ዓለም አቀፋዊ ግጭቶች ምክንያት የታቀደውን ያህል ድጋፍ አለመገኘቱን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ፣ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል፣ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩን ተከትሎ የአውሮፓ ኅብረት ባወጣው መግለጫ፣ “በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የቀጠለው ግጭት እና በደል ለተጨማሪ የሕዝብ መፈናቀል ምክንያት መኾኑ አሳስቦኛል፤” ብሏል።

የጄኒቫው መርሐ ግብር አዘጋጆች በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት “የቀውሶችን ቁልፍ ቋጠሮዎች ለመፍታት ባለድርሻ አካላትን በንቃት ለማሳተፍ ቃል መግባቱን” አመልክተዋል፡፡

ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።