የባይደን የምረጡኝ ዘመቻ እና የትረምፕ የፍርድ ቤት ሳምንታዊ ውሎዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በያዝነው ሳምንት፣ የዩናይትድ ስቴትስ 47ኛው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች፣ ዶናልድ ትረምፕ እና ጆ ባይደን በኹነቶች የተሞሉ ውሎዎችን አሳልፈዋል፡፡

ትረምፕ፣ የንግድ ድርጅታቸውን ሰነዶች አጭበርብረዋል፤ በሚል ለቀረበባቸው ክስ፣ ከሕዝብ የሚመረጡ ዳኞች መረጣ በተካሔደበት በኒው ዮርክ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡

ዴሞክራቱ ተፎካካሪያቸው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ደግሞ፣ በምጣኔ ሀብት ፍትሐዊነት ጉዳይ ከተቀናቃኛቸው ጋራ ያላቸውን ልዩነት ለማስረዳት ዘመቻ እያካሔዱ ናቸው፡፡

የቪኦኤው ስካት ስተርንስ፣ የሁለቱን ተፎካካሪዎች ውሎዎች የሚያስቃኝ ዘገባ አስተላልፏል፡፡