የራያ አላማጣ ወቅታዊ ሁኔታ

Your browser doesn’t support HTML5

በራያ አላማጣ ወረዳ ግጭት በመቀስቀሱ የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች እና በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም በግጭቱ ምክንያት መፈናቀላቸውን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ። በግጭቱ የወረዳው አስተዳዳሪ ሞላ ደርበው መገደላቸውን የዐይን እማኝ ነን፤ ያሉ ተፈናቃዮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ግጭቱ አካባቢው በሚገኙ ሚሊሻዎች የተፈጠረ መኾኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ አስተዳደራቸው በኀይል ለመቆጣጠር የሚፈልገው አከባቢ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኀይሉ አበራ በበኩላቸው፣ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች የፕሪቶርያን የሰላም ስምምነት ጥሰው የራያ አላማጣ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል፤ ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ክሥተቱ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በህወሓት አልያም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም፤ ብለዋል፡፡

ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።